የኢትዮጲያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ከሚያከንውናቸው ተግባሮች አንዱ የሆነው ይፈጠራ ስራ ምዝገባ፣ ይህንን ዝምድና የተሰኘ ፕሮጀችት መዘገበ።
ቅጅ መብት ምንድን ነው?
የቅጅ መብት ማለት አንድን የአዕምሮ ውጤት የሆነን የሥነ ጽሑፍ፣ የኪነጥበብ፣ የሥነ-ጥበብ፣ የዕደ-ጥበብ፣ የኮምፒዩተር ኘሮግራም ወይም የፎቶግራፍ ሥራ ለሠራ ግለሰብ/ግለሰቦች የሚሰጥ መብት ሲሆን የተዛማጅ መብት ማለት ደግሞ ከላይ የተጠቀሱትን የቅጅ መብት የሚያስገኙ የፈጠራ ሥራዎችን ተንተርሰው በሥራው ላይ የሚሳተፉ ከዋኞች፣ የድምፅ ሪከርዲንግ ኘሮዲውሰሮች እና የብሮድካስቲንግ ድርጅቶች የሚያገኙት መብት ነው፡፡ ማንኛውም የሥራ አመንጪ የሥራው ዓላማና የጥራት ደረጃ ግምት ውስጥ ሳይገባ ሥራው ወጥ (ኦርጅናል) ከሆነ እና ግዙፍነት ካገኘ ወይም ከተቀረፀ ሥራውን በማውጣቱ ብቻ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጥበቃ ያገኛል፡፡ የፈጠራ ሥራውን የሰራ ግለሰብ ሥራውን የማባዛት፣ የመተርጎም፣ የማመሳሰል፣ የማቀናበር ወይም ወደ ሌላ አይነት የመቀየር፣በሽያጭ ወይም በኪራይ ኦሪጅናል ሥራውን ወይም ቅጅውን የማከፋፈል፣ ኦሪጅናል ሥራን ወይም ቅጅውን ለህዝብ የማሳየት መብት ይኖረዋል፡፡